Limit this search to....

ባጭር የተቀጨ ረጅም ጉዞ (Bachir Yetekeche Rejim Guzo): መኢሶን &#
Contributor(s): Assegid, Andargachew (Author)
ISBN: 1599071118     ISBN-13: 9781599071114
Publisher: Tsehai Publishers
OUR PRICE:   $39.55  
Product Type: Paperback - Other Formats
Language: Amharic
Published: April 2020
Qty:
Additional Information
BISAC Categories:
- Biography & Autobiography | Personal Memoirs
- Biography & Autobiography | Cultural, Ethnic & Regional - African American & Black
Physical Information: 1.2" H x 6" W x 9" (1.73 lbs) 540 pages
 
Descriptions, Reviews, Etc.
Publisher Description:

'ባጭር የተቀጨ ረጅም ጉዞ፡ መኢሶን በኢትዮጵያ ሕዝቦች ትግል ውስጥ' ለንባብ ከበቃ 20 ዓመታት አልፏል። የሚተርከው የዛሬ 45 ዓመት በኢትዮጵያ ስለተካሄደው የ1966 አብዮትና በሐምሌ 1960 ስለተመሰረተው የመኢሶን ሚና ነው። ይህ የፀሐይን የሕትመት ጥራት ደረጃ በተከተለ መልኩ የተሟላ የአርትኦት ሥራን፣ አዳዲስ ታሪካዊ ፎቶግራፎችን፣ እንዲሁም የደራሲውን አዲስ መግቢያና መጠቁም ያካተተ ነው።

መፅሐፉ መኢሶን ከተመሠረተበት ጊዜ አንስቶ እስከ ነሐሴ 1969 ድረስ ያለውን የመኢሶንን ታሪክና ሚና ይመለከታል። ከ1960 እስከ 1966 በአገር ውስጥና በውጭ በህቡዕ ሲታገል ቆየ። በየካቲት 1966 እንቅስቃሴ ውስጥ ተሳተፈ። በየካቲት 1967 የታወጀው የመሬት ላራሹ አዋጅ በሥራ እንዲተረጎም ታገለ። ከሚያዝያ 1968 እስከ ነሐሴ 1969 በነበሩት 15 ወራት ውስጥ ከደርጉ ጋር ጊዜያዊ ትብብርን መሥርቶ ሠራ። በነሐሴ 14፣ 1969 ከደርጉ ተለየ።

መፅሐፉ ስምንት ክፍሎች ያሉት ሲሆን በየክፍሉ ሥር በምዕራፎች፣ በአርዕስትና በንዑስ-አርዕስት እየተዘረዘረ የቀረበ ነው። የመጀመሪያው ክፍል ከተማሪ እንቅስቃሴ ወደ ፖለቲካ ድርጅት መቋቋም የተደረገውን ጉዞና የመጀመሪያዎቹን የትግል ዘመናት ይዳስሳል። ሁለተኛው ክፍል የሚያተኩረው በቅድመ-አብዮት ዘመን በነበሩት የመኢሶን/ኢህአፓ ልዩነቶችና የፖለቲካ ትግሎች ላይ ሲሆን ሦስተኛው ክፍል ደግሞ በየካቲት አብዮት መፈንዳት፣ ሂደትና ክንዋኔ ላይ ይመለሳል። የደረሱትን ሁነቶችና ያስከተሏቸውን ውጤቶች በመዋዕለ-ዜና መልክ ለመከተል ይሞክራል። አራተኛው ክፍል በተለይ የሚመለከተው ከንጉሠ-ነገሥቱ መውርድ እስከ የካቲት የመሬት ይዞታ አዋጅ ድረስ የነበሩትን ጉዳዮች ነው። ዋናውም ጥረት ያንን ብዥ ያለ ዘመን ገለጥ ለማድረግ ነው። ክፍል አምስት ከመሬት ይዞታ አዋጅ እስከ መስከረም 1968 የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ድረስ የነበረውን "የአንድ እርምጃ ወደፊት፣ ሁለት እርምጃዎች ወደኋላ" ታ