Limit this search to....

የልጅነት መንፈስ
Contributor(s): Tilahun, Ermias (Author)
ISBN: 1087925649     ISBN-13: 9781087925646
Publisher: Ermias Woldeyesus
OUR PRICE:   $9.49  
Product Type: Paperback
Language: Amharic
Published: September 2014
Qty:
Additional Information
BISAC Categories:
- Religion | Christian Living - Personal Growth
Physical Information: 0.19" H x 6" W x 9" (0.30 lbs) 92 pages
 
Descriptions, Reviews, Etc.
Publisher Description:

ክርስቶስ ሰማይንና ምድርን ያገናኘ የማይነካካውን ያነካካ እውነተኛ መሰላል ነው። ለመሆኑ መሰላል ምንን ያሳየናል? መሰላል አንደኛ ቆመን ልንደርስበት ወደማንችልበት ከፍታ የምንወጣበት ነገር ነው። ስለዚህ መሰላል ስናይ ከፍ ያለ ነገር እንዳለ እናያለን። እግዚአብሔርና የመጥራቱ ዋጋ ባለንበት ሆነን ልንደርስባቸው የማንችል ከፍ ያሉ ናቸው። እጅጉን ከፍ ወዳለው ወደ እግዚአብሔርና ከሐሳባችን ጋር ሲነጻጸር ሰማይ ከምድር እንደሚርቅ ወደሚርቀው ሐሳቡ ለመድረስ መሰላል ያስፈልገናል። ያለንበትን ዝቅታ ርቀት ያወቀው እግዚአብሔርም ክርስቶስን ወደርሱ የምንደርስበት መሰላል አድርጎ ሰጥቶናል።


ክርስቶስን እንደመሰላል ካወቅነው የመሰላልን አሰራርና አጠቃቀም ደግሞ መረዳት ይኖርብናል። ስለዚህ በሁለተኛ ደረጃ መረዳት ያለብን መሰላል በአንድ እርምጃ ከታች እስከላይ የምንደርስበት ሳይሆን ብዙ ደረጃዎች ያሉትና ካንዱ ደረጃ ወደሌላው ደረጃ እየተራመድን የምንወጣበት መሆኑን ነው። መሰላልን መሰላል ያስባለው የእኛን እርምጃ የሚመጥኑ ብዙ ደረጃዎች ያሉት መሆኑና ረጅሙን ከፍታ በጥቂት በጥቂቱ እንድንወጣ ማድረጉ ነው። የልጅነት መንፈስ የተባለው ይህ መልእክት ይህንን ደረጃ በተግባራዊ መንገድ የሚያሳየንና ትልቅና ከፍ ያለ ወደሆነው ወደ እግዚአብሔርና ከፍ ወዳለው ሐሳቡ ደረጃ በደረጃ እንዴት እንደምንራመድ የሚመራን ነው። የተጠራንበት የእግዚአብሔር ዓላማ ገና ጌታን ስንቀበል የተፈጸመ ወይም እኛን ልጅ አድርጎ ብቻ ያለቀ ሳይሆን እነዚህ የዚህ መሳል የመጀመሪያ ደረጃዎች መሆናቸውንና ከመዳንና ከልጅነት ተነስተን ከደህንነት ከፍታ ወደ ማይጠፋ ዘርነት፣ ከማይጠፋ ዘርነት ወደ ልጅነት ክብር፣ ከልጅነት ክብር ወደ ልጅነት መገለጥና ከዚያም በሚገለጡት ልጆች ወደሚሆነው የፍጥረት ነጻነት እያንደረደረ የተወሰነልንን ከፍታ ያሳየናል።